ከአንቺ ወይም ከአንተ ጋር በአንድ ላይ ነን፤ በጎዳናህ ላይ

በአንድ ጣሪያ ስር ምክር፣ መመሪያ እና ድጋፍ ለመስጠት የአልማ ማዕከላት የቤተሰብ ውስጥ ጥቃትን ለመከላከል የተነሱና የተቋቋሙ ናቸው።
ያለ ቅድመ ሁኔታ፣ ቁርጠኝነት ወይም ክፍያ ሳንጠይቅ ቀንና ሌሊት በሳምንቱ 24/7 ስዓታት ለእርስዎ ለመርዳት እዚህ እንገኛለን።

ከአንቺ ወይም ከአንተ ጋር በመተዋወቃችን ደስ ይለናል

አስተማማኝና ደህንነቱ በተጠበቀ ቤት ውስጥ ያለ ፍርሃት ያለምንም ግጭት በሌለበት ሰላም በሰፈነበት ቤት መኖር  ለሁላችን ያሰፈልገናል፡፡

  ለአንቺም ሆነ ለአንተ ያስፈልጋል

ቤትዎ የተጠበቀ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ስለመሆኑ ጥርጣሬዎች ወይም የጥያቄ ምልክቶች በሚያጋጥሙበት ጊዜ እና እንዲሁም መልሱ ለእርስዎ ግልጽ በሆነባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን መልስ ለመስጠት የአሎማ ማእከሎች የተቋቋሙ ናቸው።

በአሎማ ማእከላት የእርስዎን ልዩ ሁኔታ አንድ ላይ ለማጣራትና ለማወቅ እንዲሁም የመጀመሪያ አጠቃላይ እርዳታን 24/7 ልንሰጥዎ እንችላለን፡፡ በቀን በሁሉም ሰዓታት እና በሳምንቱ ቀናት ፣ በማዕከሉ ቢሮ ሆነ   ወይም በርቀት ምላሽ በመስጠት ፣ በተቻለ መጠን በማህበራዊ መ/ቤት ወይም በፓሊስ ጣቢያ አገልግሎት ለመቀበል ፋይል ሳትከፍቱ ከእኛ ዘንድ አገልግሎት የመቀበል አማራጭ አላችሁ፡፡

በማዕከሎች ውስጥ, በአንድ ጣሪያ ስር, የተለያዩ አገልግሎቶችን እና ሊረዱዎት የሚችሉ የመጀመሪያ እርዳታዎችን እናቀርብልዎታለን፡፡  እርዳታዎች እና በስሜት ድጋፍ፣ በህግ ድጋፍ እና የመብት አጠቃቀምን በተመለከተ ሊደረስዎት ከሚችል መረጃ፣ ምክር እና መመሪያ ጀምሮ፣ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሳይሄዱ፣ ስሜታዊ እና አካላዊ አቅርቦትን  በማእከሉ ቢሮ  ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። አስፈላጊ ከሆነ በማዕከሉ ውስጥ የአደጋ ጊዜ መጠለያን ጨምሮ ጥበቃ ያካትታል፡፡ በቀጣዮ ሂደት ውስጥ፣ እንደ ልዩ ፍላጎቶችዎ፣ ነባሩን ሁኔታ ለመለወጥ እና አዲስ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ህይዎትን ለመቀጠል ለመጀመር በሚያስችል መንገድ በማህበረሰቡ ውስጥ እርስዎን ከክትትል እንክብካቤ ጋር በማፈላለግ እና በማገናኘት እንረዳዎታለን።

የሚስምማ ተደራሽ እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት፣ ማዕከላቱ ማህበራዊ ሰራተኞችን፣ የግል ረዳቶችን፣ የፖሊስ መርማሪዎችን እና የስነ-አእምሮ ሃኪምን እና የህግ ድጋፍን ያካተተ ባለብዙ ሙያዊ ቡድን አሏቸው። የአሎማ ማዕከላት በመላ አገሪቱ ይገኛሉ፡- አኮ ፣ ቤት ሸመሽ ፣ ሪሾን ለጺዮን እና ቢኤር ሸቫ ( ሀልቱ ከተሞች ሪሾን ለጺዮን እና ብ ኤር ሼባ በ2023 ዓ/ም ውስጥ ሥራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃሉ)።

በተጨማሪም ማዕከላቱ በቤተስብ ውስጥ በሚፈጥር ብጥብጥ የሚመለከቱ መስኮች  ሙያዊ የምክር አገልግሎት የሚያገኙበት ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎች አድራሻ ናቸው፡፡

ሁላችንም ለአስተማማኝ፣ የተረጋጋ እና ደስተኛ ህይወት እድል ይገባናል።

ለአንቺ ሆነ ለአንተ

እኛ እዚህ ያለነው ለዚያ ነው፣ ከእርስዎ ጋር!

ማዕከላቱ የተቋቋሙት በቤተሰብ ውስጥ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስወገድ  ፣ ድጋፍ ለማድረግ የተለያዮ ቢሮውችን ያቀፈ የብሔራዊ  ፕሮግራም በማህበራዊ ቢሮ እና በህብረተሰቡ ደህነት ቢሮ  ከመንግስት ቢሮዎች ጋር በመተባበር እና በመሪነት ብሎም ከሌሎች ከመንግስት ሚኒስቴሮች ቢሮ ጋር በመተባበር የሀገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስትር ቢሮ ፣ የፍትህ ሚኒስቴር ፣ የአካባቢ የማዘጋጃ ቤቶች ባለስልጣናት ፣ ራሺ ፈንድ እና የቢቱዋህ ሌኡሚ መ/ቤት ጋር በመተባበር ማእከላቶቻን ይሰራሉ.