ጥያቄዎች እና መልሶች
ጠቃሚ እና የተለመዱ ጥያቄዎችን እና መረጃ ሰጪ መልሶችን አዘጋጅተናል
ይሄን ጉዳይ አስቀድሞ መግለጽ አያስፈልግም፡፡
አብረን የምናደርገው አንዱ ክፍል አንዳንድ ጊዜ ብቻውን ለመስራት አስቸጋሪ የሆነ ማብራሪያ ነው። ማብራሪያው አስገዳጅ ባልሆነ የስልክ ምክክር ሊጀመር ይችላል።
አንቺ ወይም አንተ ባሉበት ግንኙነት ውስጥ የሆነ ነገር የተለመደ ወይም ትክክል እንዳልሆነ ከተሰማማችሁ ወደ እኛ ማመልከቻ ለማቅረብ ጊዜው አሁን ነው።
እንደዚህ እና እንደዚህ አይነት ፍቺዎች ትርጉም መስጠት አያስፈልግም ፡፡ የአሎማ ማእከል ለአንችም ሆነ ለአንተ ትክክለኛ ቦታ መሆኑን እንዲረዱ ልንረዳችሁ እንችላለን፡፡
ማዕከሎቹ በቤተሰብ ውስጥ ጥቃት ለተጠቂዎች ምላሽ ይሰጣሉ፤ እና ግንኙነቱ ጸቡ ወይም ጥላቻው ኃይለኛ ስለመሆኑ ጥርጣሬ ላለው ወይም ለማያውቅ ለማንኛውም ሰው ሴቶች እና ወንዶች ድጋፍ ያደረጋል፡፡
ሁሌም እና በእንዳንዱ በአሉማ ማዕከል እርዳታ መቀበል ትችላላችሁ፡፡
የኦሎማ ማእከላት በቀንና ሌሊት በሳምንት 7 ቀናት 24 ስዓታት ቅድሜ ሰንበትና አመት በዓላት ጭምሮ ክፍት ሆነው አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
በአሁኑ ውቅት በአኮ ከተማ እና በቤት ሼሜሽ ከተማ ማእከላቱ ተከፍተው እየሠሩ ነው፡፡ በቀጣይነትም በሪሾን ለጺዮን ከተማ እና በብኤር ሼባ ከተማ ማዕከላቱ ይከፈታሉ፡፡
በአካል፣ በማንኛውም ማእከል፣ በማንኛውም ጊዜ ወደ እኛ መምጣት ይችላሉ፣ እንዲሁም አገልግሎት እና እርዳታ ከርቀት ማግኘት ይችላሉ – ለአንቺ ሆነ ለአንተ ተገቢ እና ትክክል የሆነው አግልግሎት ይሰጣችኋል፡፡
አጃቢ እና እርዳታን በርቀትም እንሰጣለን ምክንያቱም አገልግሎታችንን እና የምንሰጠውን እርዳታዎች ከአንቺ ወይም ከአንተ ጋር ፍላጎት ጋር ማስማማት ለእኛ አስፈላጊ ነው::
ለአንቺም ሆነ ለአንተ የሚያስፈልጋችሁ እኛን ማነጋገር ብቻ ነው።
ከእኛ ጋር የሚገናኝ ወይም ለእኛ ማመልከቻ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው በምንም መልኩ ማንነቱን ሳይገልጽ እንኳን አገልግሎት ያገኛል።
የመጀመሪያ ስምሽን ወይም ስምህን እንኳን ሳይቀር ማንኛውንም የግል ወይም መለያ ዝርዝር መረጃ መስጠት የለብሽም ወይም የለብህም፡፡
በተጨማሪም መረጃው ለከቴውም በሚስጥር ይጠበቃል ፤ እንደዚሁም ያለ አንቺ ወይም ያለአንተ ፈቃድ እና ፊርማ መረጃን ለማንኛውም አካል ማስተላለፍ የተከለከልን ነው።
ለአንቺ ወይም ለአንተ የማይስማማውን ነገር የማካፈል ግዴታ የለበትም ፣ እንዲሁም አሁን ውሳኔ ለማድረግ ወይም እስካሁን ለአንቺ ወይም ለአንተ የማይስማማውን ነገር የማድረግ ግዴታ የለበትም።
አይደለም ፤ ከእኛ ዘንድ አገልግሎት ለመቀበል በሚል ለፓሊስ ቅሬታ ማቅረብ ግዴታ የለበትም፡፡ በሚከተለው አንቺ ወይም አንተ በኦሎማ ድርጅት ለሚገኙት ፓሊስ መርማሪዎች ቅሬታ ማቅረብ ትችላላችሁ ፤ ወደ ፓሊስ ጣቢያው መምጣት አሰፈላጊ አይደለም
አንቺም ሆነ አንተ ከእኛ ዘንድ የመጀመሪያ መረጃ ፣ አጃቢ እና እርዳታ ታገኛላችሁ።
እንደፍላጎትሽ ወይም ፍላጎትህ እና ፍላጎትሽ ወይም ፍላጎትህ የሚስማማ ለረጅም ጊዜ ሂደት አብሮህ ከሚቆዮት ድጋፍና እጃባ ከሚያደርጉልህ አካላት ጋር እንድተገናኙ እኛ እንረዳችኋለሁ
ወዲያውኑ ለሕይወት አስጊ ከሆነ፣ እባክሽን ወይም እባክህ በአስቸካይ ለፓሊስ በስልክ ቁጥር 100 ደውሉ።
ከዚህ ጎን ለጎን አስቸኳይ እና ከባድ ውሳኔዎች መወሰድ እገቢ ስለሆነ የእኛ ቡድናችን በስልክ ሊያግዝሽ ወይም ሊያግዝህ ብሎም ሊመራችሁ ይችላል።
አስቸጋሪ እና አስጨናቂ አጋጣሚ ሁኔታዎች ፣ አንዳንድ ጊዜ አስጊ እና አስፈሪ ናቸው፡፡ ስልሆነም ብቻቸውን ለማለፍ ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሁኔታውን በተሻለ መንገድ አንችን ወይም አንተን ለመጠበቅ እና ደህንነታችሁን ለመጠበቅ በሚያስችል መንገድ እናንተን ለመረዳት ደስተኞች እንሆናለን፡፡
ማዕከሉ በአጥር የተከበበ ነው ፣ ሁል ጊዜ የተቆለፈ እና የደህንነት ካሜራዎች አሉት።
ከማዘጋጃ ቤት የስልክ መስመር ጋር የተገናኘን ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከማዘጋጃ ቤት ፖሊስ ጣቢያ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እናደርጋለን። እኛ ከአንቺ ወይም ከአንተ ጋር በአንድ ላይ የአደጋውን ደረጃ እናጣራለን ።
አንችን ወይም አንተን በሚመቻችሁ አንጻር እና መንገድ ለመርዳት ካለን ፍላጎት የተነሳ አገልግሎቱን በ”አሎማ” ማእከላት ከወትሮው በተለየ መልኩ ለመስራት ወስነናል።
አሎማ ቅዳሜ እና በዓላትን ጨምሮ ዘውትር በየቀኑ እና በሰዓቱ ክፍት እና የሚገኝ አገልግሎት ነው።
ምንም እንኳን እስካሁን ምንም አይነት መደበኛ ተቋም (የበጎ አድራጎት ወይም የፖሊስ) ግንኙነት ባይኖርሽም ወይም ባይሆርህም እና ስለራስሽ ወይም ስለራስህ ምንም አይነት ምቾት የማይሰጥልሽ ወይም የማይሰጥህ ዝርዝር ነገር ሳይነግሩን እንኳን ሙሉ አገልግሎት እና መልስ እንሰጣችኋለሁ።
ከእኛ ጋር የመጀመሪያ ጉዳዮን የማጣራትጥያቄ እና አስተሳሰብ ብቻ ማድረግ ወይም ተግባራዊ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ድጋፍ መቀበል ይቻላል – የአንቺ ሆነ የአንተ ውሳኔ ነው!
በአንዳንድ ሁኔታዎች እና እንደ ሠራተኛው ውሳኔ ፣ በቦታው ላይ ብዙ ምሽቶች የመቆየት እዚያው የመተኛት አማራጭ አለ:: ስለሆነም ለአንቺ ወይም ለአንተ ከነልጆቻችሁ ጋር በሁሉም መልኩ ለጥቂት ቀናት ቆይታ የሚያስፈልጋችሁ ነገሮች ሁሉ አለን።
በአሎማ የአንድ ጊዜ እርዳታ እንደሚያገኙ ማወቅ አስፈላጊ ነው ፣ ይህም ለረዥም ሂደት መነሻ ሊሆን ይችላል ፣ እና ይህ የአንቺ ወይም የአንተ ምርጫ ከሆነ በኋላ ከሚረዱት አስፈገላጊ ከሆኑት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንድተገናኙ እናግዛችኋለን፡፡ ከአንቺ ወይም ከአንተ ጋር አስፈላጊ የሆነው ነገር ከእኛ ጋር መገናኘት ፣ መነጋገር ወይም ወደ እኛ ዘንድ መምጣት ነው፡፡
በእርግጠኝነት አዎ! በማንኛውም ዕድሜ ላይ ካሉ ልጆች ጋር መምጣት ይችላሉ:: የቤተሰብሽ ወይም የቤተሰብህ ልጆቻችሁ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ለተወሰኑ ቀናት ሊረዱዷችሁ አስፈላጊ የሆኑት ሁሉም ነገር አለን ። በአንዳንድ ሁኔታዎች ለብዙ ምሽቶች የመተኛትና የመኖርያ ዕድሎች በሠራተኞች ውሳኔ ፣ ትኩስ ምግብ ፣ ከአጃቢ ቡድን እና ሌሎችም ወዘተ… ለእናተ የሚሰጡ እርዳታዎች አሉን። .
በእርግጠኝነት አዎ ፣ ስለምትወዷቸው ሰዎች ስለሚያሳስባችሁ ጉዳይ ባስመለከተ ከእኛ ጋር መገናኘት እና መወያየት ትችላላችሁ።
በጎ ፈቃድ እና መጨነቅ በጣም አስፈላጊ ናቸው ፣ እንዲሁም የባለሙያ ድጋፍ ማግኘትም አስፈላጊ ነው::
እኛ ሁኔታውን ለመረዳት እና እናንተን መርዳት እንድንችል እናንተ ምን ያህል እንደተጨነቃችሁ በተቻለ መጠን ለመረዳት ፣ በተክክለኛ መልኩ እናንተን ለመርዳት የተሻለውን እርዳታ ለመለገስ እንፈልጋለን፡፡